ዲፌንድ ኢትዮጵያ በአውሮፓ የስራ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ የኢፌዴሪ አምባሳደሮች የዕውቅና ሽልማት ሰጠ

ዲፌንድ ኢትዮጵያ የአውሮፓ ግብረ ሀይል በአውሮፓ የስራ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁና ለግብረ ሀይሉ እንቅስቃሴዎች ድጋፍ ላደረጉ የኢፌዴሪ አምባሳደሮች የዕውቅና ሽልማት ሰጠ።

ግብረ ሀይሉ የዕውቅና ሽልማቱን ያበረከተው ለክቡር አምባሳደር ዘነበ ከበደ በስዊዘርላንድ፣ ኦስትሪያ፣ ሀንጋሪና ሩሜንያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር፣ ለክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በጀርመን፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ፖላንድ፣ ስሎቫኪያና ዩክሬን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም ለክቡር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፓርቹጋል፣ ሆሊሲና ሞናኮ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሲሆን፣ ክቡራን አምባሳደሮቹ በየሀገራቱ በነበራቸው ቆይታ ግብረ ሀይሉ ላካሄዳቸው ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ድጋፍ በማድረግ ስላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናውን መግለጹን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ምንጭ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት